restoring our biblical and constitutional foundations

                

ቤተክርስቲያንን የሚገዛው ማነው?

 David Alan Black  

ኢየሱስ በቅዱሳን ጉባዔ የሚያገለግለው በሰማዊ ነው፡፡ ‹‹ቤተክርስቲያኔን እመሰርታለሁ›› ያለው እርሱ ነው (ማቴ 16፡18) ነገር ግን ኢየሱስ ቤ/ክቲያንን የመሰረተው እንዴት ነው? በምን ሥልጣን ነው? ቢያንስ ሰባት ነገሮች ሊባሉ ይችላሉ፡፡

1. ክርስቶስ ብቻ የቤ/ክ ራስ ነው፡፡ እርሱ ብቻ ዋና መጋቢ ነው(ማቴ 28፡18) ቆላ 1፡18 ኤፌ 4፡5 41 ጴጥ 5፡2

2. የክርስቶስ ሥልጣን በጉባዔው የተገለጠው በስጦታዎችና በመንፈስ ቅዱስ አገለግሎት በኩል ነው፡፡ ሁሉም መንፈስ ቅዱስን የተሞሉ አማኞች ክህነትና ተጠያቂነታቸውም በቀጥታ ለራስ (ለኢየሱስ) ነው (ሮሜ 14፡4 2 ጢሞ 2፡5)፡፡ በተጨማሪም ሁሉም አማኞች ስጦታዎች አሉአቸው፡፡ እንዲሁም አንደየስጦታቸው በጉባዔውና ጉባዔውን ማገልገል ይችላሉ (ሮሜ 12፡3-8 1ቆሮ 12-4 ኤፌ 4፡7 16)፡፡ አዲስ ኪዳን ስለካህናትና (ቀሳውስትና) መዕመናን ልዩነት የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ሁሉም ምዕመናን ሙሉ የሆነ የክህነት አገልግሎት ያላቸው ናቸው፡፡

የተለያዩ ወንድሞች ቤ/ክንን ያስተምራሉ እንዲሁም ህዝቡ ጥያቄ ልጠይቃቸው ተፈቅደለታል፡፡ የራሳቸውን ሀሳቦች በመንፈስ ቅዱስ አመራር ሥር ሆነው መጨመር ይችላሉ፡፡ (ሐወ 20፡7-1ቆሮ 14፡29-35)

3.  በእያንዳንዱ ጉባኤ የተወሰኑ ወንድሞች ብቻ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የተሰጣቸው ብቻ አይደሉም፡፡ ነገር ግን እራሳቸውም በቤ/ክን የክርስቶስ ስጦታዎች ናቸው (ኤፌ 4፡11)፡፡ ዋናው አገልግሎታቸውም የእግ/ርን ቃል ማስተማርና ያሉትን ቅዱሳን አብረው ለአገልግሎት ሥራ ማብቃት ነው፡፡ (ኤፌ 4፡12) “መጋቢና አስተማሪዎች” የሚለው አገላለጽ (ኤፌ 4፡11) የሚያሣየው ሥፍራን (ሥልጣንን) ሳይሆን ሥራን ወይም ተግባርን ነው፡፡ የቤ/ክ “ቢሮ” (office) የተመሰረተው በሰዎች ባህል ላይ በተሳሳተ ትርጉም ላይ ነው (ለምሳሌ 1 ጢሞ 3፡1 ጳውሎስ የተናገረው ስለ “ኤጵስ ቆጰስናት” እንጂ ስለ ጳጳስ ሥልጣን አይደለም በKJV መጽሐፍ እንደተጠቀሰው)፡፡

4. በህዝቡ መካከል ያሉ መሪዎች የቤ/ክ አባል ናቸው እንጅ የበላዮች (ገዥዎች) አይደሉም (ኤፌ 1፡1)፡፡ በዕድሜ የቆዩና በንፈሳዊነትም የበሰሉ ወንድሞች (ሽማግሌቻች) በመሆናቸውም ለእግ/ር ድምጽ ትኩረት የሚሰጡና የሚታዘዙ ናቸው፡፡ ተግባራቸው ጉባኤውን መቆጣጠር ሲሆን ጉባኤው ደግሞ በትክክል ልምምዳቸውንና ስጦታዎቻቸውን ማወቅ አለበት (ሐዋ 20፡28 1 ተሰ 5፡12-13)፡፡ እነዚህ መሪዎች የሚነሱት ህይወታቸውና ባህርያቸው ከሚታወቅበት ከአጢብያ ቤ/ክ ነው (ሐዋ 14፡23, ቲቶ 1፡5)፡፡

5. ሽማግሌዎች በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተሾሙ ሲሆኑ (ሐዋ 20፡28) መሰረቱም ብስለታቸው ስጦታቸውና በተለይም ባሪያቸው ነው (1ጢሞ 3፡1-7,ቲቶ1¸5-9)፡፡

ቤ/ክነት ለሽምግልናቸው እውቅና ይስጡት እንጂ ሽማግሌዎችን አይሾሙም፡፡

ወንዶች የመቆጣጠርን ሥራ የሚሰሩት ሽማግሌዎች ስለሆኑና የመጋቢነት ሥጦታ ስለተሰጣቸው ነው፡፡

6. አዲስ ኪዳን ሁል ጊዜ ስለ ኤጰሶ ቆጶስት  የሚያመለክተው ብዙ ቁጠር ነው (ፊል1፡1 1 ጢሞ 4፡17 ዕብ 10፡17 ያዕ 5፡14 1ጴጥ 5፡1-2)፡፡ እኔ ከመጋብ ጋር ስላለች ቤ/ክ ምንም አላውቅም፡፡ ለምሳሌ የኤፊሶን ቤ/ክ ያላት ብዙ ቁጥር ያላቸው ሹማግሌዎች እንጂ አንድ “መጋብ” አይደለም (ሐዋ 20፡17) አንዲሁም በራዕ 2፡1 ያለው “መልአክ” አንድ መጋብ የሚለውን አሰራር ለመደገፍ መጠቃም አይቻልም፡፡

7. ብዙ ጊዜ አንድ ሹማግሌ ከልምምድና ከስጦታው የተነሳ በህዝብ ላይ የበለጠ ተጽዕኖ ሊያመጣ ይችላል ቢሆንም እንደዚህ አይነት ሹማግሌ ግን “ዋና መጋቢ” (ራስ) ሳይሆን ከሽማግሌዎች ጋር አብሮ ያለ (የሚሰራ) አንዱ ሽማግሌ ነው (1ጴጥ 5፡1)፡፡ ኢየሱስ ከወንድሞች የሚለያቸውን የማዕረግ ስያሜዎችን ለራሳቸው እንዲያደርጉ ተከታዮቹን አስተሞሯል (ማቴ 23፡6-12 ማር 10፡35-45)፡፡

እነዚህ መመሪያዎች በአስተያየት ደረጃ ብቻ የሚቀሩ አይደሉም፡፡ የአከሉ ራስ በሆነው ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመገዛት በደስታ የሚንለማመዳቸው መሆን አለባቸው፡፡

እነዚህን መመሪያዎችን ታሳቢ ባደረገ አንዳንድ ጥያቄዎችን እራሳችንን በሚገባ መጠየቅ አለብን፡-

1. አዲስ ኪዳን ምንም ልዩነት ባላሳየበት ለምንድነው ጉባዔዎቻችን መሪነትን በስልጣን ተዋረድ ‹‹ዋና መገቢ›› ‹‹ረዳት መጋቢ››… ወዘተ በማለት የሚከፋፈሉት?

2. ለምንድነዉ አብዛኞቹ ቤ/ክርስቲያኖችን የራሳቸውን ሰው በማሳደግና በማሰልጠን ፈንታ ከደረጃቸው ውጭ የሆኑትን ብቃት ያላቸውን መራዎች የምፈልጉት?

3. ለምንድነው ቤ/ክየኖቻችን ለምዕመኖቻቸው ስጦታቸውን (የማስተማር ስጦታ ጭምር) እንዲለማመዱ በቂ እድል የማይሰጡት?

4. ሁሉም አማኞች ካህናትና ስጦታ ያላቸው ከሆኑ ለምንድ ነው አብዛኛው ጉባኤያችን የመተናነጽ ኃላፊነት በቀጥታ በባለሙያ ‹‹ካህናት›› ላይ የሚያደርገው?

ወዳጆቼ እግዚአብሔርን ለነፍሳችን እንደምናመልከው ለቤ/ክኖቻችንም እናምልከው፡፡ ምናለባትም የቤ/ክ ሁኔታ በትክክል የሚለካው በአመራሩ ነው፡፡ በእውነት ሁሉ መጋቢዎች ሁል ጊዜ ያለጥርጥር ‹‹ክርስቶስ የቤ/ክርስቲያናችን ራስ ነው›› እንድሉ እመኛለሁ፡፡

June 12, 2010

David Alan Black is the editor of www.daveblackonline.com.

Back to daveblackonline