|
|
አናባፕቲስቶችን ለምን ወደድኳቸዉ የ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አናባኘቲስቶች ክርስቶስን ስለመከተል ብዙ የሚያስተምሩን ነገር አለ፡፡ ደቀመዛሙርትነት-የክርስቶስን ምሳሌነት መከተል ዋናው አናባኘቲስቶች የእምነት ህይወትን የሚገልጠበት መመዘኛ ነው፡፡ አናባኘቲስቶች የቆሙላቸው ነገሮች ከዚህ ቀጥሎ ያሉ ናቸው፡፡ የሚያምኑት፡- - በመግዛት ፈንታ ማገልገል - በመለያየት ፈንታ የልዩነትን ግድግዳ ማፍረስ፣ - በቤ/ክ የሥርዓት ባህል (ትውፊት) ፈንታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጣን፣ - በሥልጣን ተዋረድ የበላይና የበታች መሆን ፈንታ ወንድማማችነት - በሳይፍ ፈንታ ፎጣ - በመጋቢ ፈንታ የክርስቶስን ራስነት - በጦርነት ፈንታ የሠላም መንገድ - ቤ/ክንን እንደ ድርጅት በማየት ፈንታ እንደ ሕያው አካል መቀበል - በፖለቲካ መንግሥት ፈንታ የእግዚአብሔር አገዛዝ - በሃይማኖተኛነት ፈንታ የውነተኛዋ ዓለም አቀፋዊነት ቤ/ክ - ከሥርዓት ኃይል ይልቅ የመከራ ኃይል - መጽሐፍ ቅዱስን የሥነ መለኮት ምሁራን መጽሐፍ በማድረግ ፈንታ የቤ/ክ መጽሐፍ አድርጐ መቀበል - ለአለቆችና ኃይላት ታማኝ ከመሆን ይለቅ ለሰማያዊ ዜግነታቸው ታማኝ መሆን - በመዋቅሮች ግፍት ካለ የቤ/ክ ህይወት ይልቅ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ያተኮረ ሕይወት - በክርስቲያን ብቻ ተወስኖ ከመቅረብ ይልቅ ለህዝቦች ብርሃን መሆን - መከራን በማምጣ ፈንታ መከራ መቀበል - ስለ ክርስቶስ ከማወቅ ብቻ ይልቅ ክርስቶስን ማወቅ - ሙት በሆነ ቀጥተኛ /እውነተኛ ትምህርት ፈንታ የሚሰራ እምነት (በሁለቱም አቅጣጫ) - ፀጋን እንደ ሥነ-መለኮት ቀኖና ፈንታ እንደ ሕያው እውነታ፣ - ከተሾሙት አገልግሎት ብቻ ይልቅ የእያንዳንዱ አባል አገለግሎት - በመጠመቅ ፈንታ በክርስቶስ መጠመቅ - በስም ብቻ ከገነነ አንድነት ይልቅ በኑሮ የሚገለጥ አንድነት፣ - የተገለሉትንና የተጣሉትን ችላ በማለት ፈንታ መቀበል፣ - በሥነ አፈታት እውቀት ፈንታ የሥነ አፈታት መታዘዝ፣ June 12, 2010 David Alan Black is the editor of www.daveblackonline.com. |